ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ለከፍተኛ Deriv P2P ደረጃ እንዴት ብቁ መሆን እችላለሁ?

ከጊዜ ወደ ጊዜ ንቁ እና ታማኝ ተነጋዳይ መሆንዎን በማሳየት ደረጆችን ይወጣሉ። 5 ነገሮችን እንመለከታለን፦

1. በ Deriv P2P ላይ ያለዎት ጊዜ። ይህ ወደ P2P ከተቀላቀሉበት ጊዜ ጀምሮ ያለፉት ቀናት ቁጥር ነው። ሊቸኩል አይችልም፣ ስለዚህ መድረኩ ላይ የሚቆዩ ተጠቃሚዎችን ይሸልማል።

2. የህይወት ዘመን ልውውጥ (Lifetime turnover)። ይህ ከተቀላቀሉበት ጊዜ ጀምሮ ያጠናቀቁዋቸው ሁሉም የP2P ትዕዛዞች፣ ግዢም ሽያጭም ጨምሮ፣ ጠቅላላ ዋጋ ነው።

3. የ30 ቀናት ልውውጥ፦ ይህ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ያጠናቀቁዋቸው ሁሉም የP2P ትዕዛዞች፣ ግዢም ሽያጭም ጨምሮ፣ ጠቅላላ ዋጋ ነው።

4. ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ያለ የማጠናቀቅ መጠን። ይህ በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቁ ትዕዛዞችዎ መቶኛ ነው። የሚያቋርጧቸው ወይም በጊዜ ባለመገባደድዎ የሚያልፉ ትዕዛዞች የማጠናቀቅ መጠንዎን ይቀንሳሉ።

ምሳሌ፦ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ 20 ትዕዛዞችን አስቀምጠዋል። 18ቱ ተጠናቀዋል፣ 1ዱን አቋርጠዋል፣ 1ዱም ጊዜው አልፎበታል። የማጠናቀቅ መጠንዎ 18 ÷ 20 = 90% ነው።

5. የደንበኛ ቁጥር፦ ከተቀላቀሉበት ጊዜ ጀምሮ ግብይት ያደረጉባቸው የደንበኞች ቁጥር።

  • መስፈርት — ብሮንዝ — ሲልቨር — ጎልድ — ዳይመንድ
  • ዝቅተኛ ከተቀላቀሉ ጀምሮ ያሉ ቀናት — - — 45 — 90 — 180
  • ዝቅተኛ የህይወት ዘመን ልውውጥ (USD) — - — 15,000 — 50,000 — ያልተገለጸ
  • ዝቅተኛ የ30-ቀን የማጠናቀቅ መጠን — - — 80% — 90% — 98%
  • የደንበኛ ቁጥር — - — - — 10 — 20
  • የ30 ቀናት ዝውውር/ልውውጥ — - — - — 5,000 — 15,000

ጠቃሚ መረጃ

  • ለደረጃ ሁሉንም መስፈርቶች ማሟላት አለብዎት፣ ከፊሉን ብቻ አይደለም
  • ደረጆች በተንከባላይ 30 ቀናት መሠረት ይገመገማሉ
  • ከደረጁ መስፈርቶች አንዱ ወይም ከዚያ በላይ ካልተሟሉ ደረጆች ወደ ታች ሊወርዱ ይችላሉ፣ ለምሳሌ የሲልቨር ተጠቃሚ የ30 ቀን የማጠናቀቅ መጠናቸው ከ80% በታች ከወረደ ወደ ብሮንዝ ሊወርድ ይችላል።

በፍጥነት ለመውጣት ምክሮች

  • ለማጠናቀቅ ያሰቡዋቸውን ትዕዛዞች ብቻ ያስቀምጡ። ማቋረጥ የማጠናቀቅ መጠንዎን ይጎዳል።
  • ትዕዛዞች እንዳያልፉ በፍጥነት ይክፈሉ እና ይልቀቁ።
  • አለመግባባት እንዳይፈጠር አስገራሚ ነገሮች እንዳይኖሩ ትዕዛዝ ከመስጠትዎ በፊት የማስታወቂያውን ውሎች ያንብቡ።

አሁንም እገዛ ይፈልጋሉ?

WhatsApp