ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የግብይት ሥነ ልቦና፦ ብልህ ውሳኔዎችን ለመወሰን ስሜትዎን መቆጣጠር

5
ደቂቃ ንባብ
ከበስተጀርባ የሻማ ቻርት (candlestick) ክፍሎች ያሉት ባለ 3D አንጎል፣ በግብይት ሥነ ልቦና ውስጥ የስሜት ቁጥጥርን የሚያመለክት።

ግብይት ስሜታዊ ሊሆን ይችላል፣ ይህም ተፈጥሯዊ ነው። ግብይት እንደ ስሜታዊ ሮለር ኮስተር ሊሰማ ይችላል። ትልቅ ትርፍ የማግኘት ደስታ፣ ኪሳራ የሚያስከትለው ብስጭት፣ ቀጣዩን አጋጣሚ ለመያዝ የሚኖር ጥድፊያ። ሁሉም የጨዋታው አካል ነው። ነገር ግን ልምድ ያላቸው ነጋዴዎች የሚያውቁት አንድ ነገር ቢኖር ስሜት ትልቁ ጠላትዎ ሊሆን እንደሚችል ነው።

መረጋጋትና ሰከን ማለት ጥሩ ባሕርይ ብቻ አይደለም፤ ለረጅም ጊዜ ስኬት አስፈላጊ ነው። ስሜት እንዲቆጣጠርዎ መፍቀድ ወደ ችኮላ ውሳኔዎች፣ ከፍተኛ አደጋዎች እና እንዲሁም ትላልቅ ኪሳራዎች ሊያደርስ ይችላል። ስለዚህ ስሜትዎን መቆጣጠር ለምን ወሳኝ ለውጥ እንደሚያመጣና እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ እንነጋገር።

‍

ከልክ በላይ ግብይትን ከመጀመሩ በፊት ያቁሙት

ወደ ኋላ ማለት እንዳለብዎ እያወቁ እንኳ መገበያየት ለመቀጠል ጉጉት ተሰምቶዎት ያውቃል? ይህ ከልክ በላይ ግብይት (overtrading) ይባላል። ነጋዴዎች በጣም ብዙ ግብይቶችን ሲያደርጉ ወይም በአንድ ፖዚሽን ላይ ከመጠን በላይ ገንዘብ ሲያውሉ ይከሰታል። እና ምን እንደሆነ ያውቃሉ? ሁልጊዜ ማለት ይቻላል በስሜት የሚቀሰቀስ ነው፤ ከኪሳራ ለማገገም መሞከርም ይሁን በተከታታይ ስኬት ደስታ መመራት።

የገበያ ሁኔታዎችም ሊያታልሉዎት ይችላሉ። ዋጋዎች በፍጥነት መንቀሳቀስ ሲጀምሩ እንቅስቃሴውን ለመያዝ ብቻ መግባት ያጓጓል። ነገር ግን ግልጽ እቅድ ከሌለ ከመንገድዎ የሚያስወጡና አላስፈላጊ አደጋ ላይ የሚጥሉ የችኮላ ውሳኔዎችን ሊወስኑ ይችላሉ።
‍

ከልክ በላይ ግብይትን እንዴት መከላከል ይቻላል? ዲሲፕሊን ይኑርዎት

  • የግብይት እቅድን ይከተሉ። ጠንካራ እቅድ የተረጋጉና ትኩረት ያደረጉ ሆነው እንዲቆዩ ያደርግዎታል።
    ‍
  • ፖርትፎሊዮዎን ያለያዩ። እንቁላሎችዎን በሙሉ በአንድ ቅርጫት ከማስቀመጥ ይልቅ ካፒታልዎን በተለያዩ ንብረቶች ላይ ያሰራጩ።
    ‍
  • ካፒታልዎን ይቆጣጠሩ። ለማግኘት ተስፋ የሚያደርጉትን ሳይሆን ማጣት የሚችሉትን ብቻ ይገበያዩ።
    ‍

የአደጋ ተጋላጭነትን ይቆጣጠሩ

አደጋ የግብይት ዓለም አካል ነው። ማምለጫ የለውም። ስሜት ግን ከሚገባዎት በላይ አደጋ እንዲወስዱ ሊገፋፋዎት ይችላል።

ለምሳሌ እየጨመረ የሚሄድ (bullish) ገበያን እንውሰድ። ዋጋዎች እየጨመሩ ሲሄዱ ነጋዴዎች እድሉ እንዳያመልጣቸው መጨነቅ ይጀምራሉ። እድል የማምለጥ ፍርሃት (FOMO) ሰዎች ነገሮችን በጥልቀት ሳያስቡ ወደ ግብይት እንዲገቡ ሊያደርግ ይችላል። ከዚያም ስግብግብነት ይጀምራል፤ የበለጠ ትርፍ ተስፋ በማድረግ ፖዚሽኖችን ለረጅም ጊዜ ይይዛሉ። ነገር ግን እንደምናውቀው ገበያው ሁልጊዜ ቸር አይሆንም፤ እነዚያ ትርፎችም እንደመጡ በፍጥነት ሊጠፉ ይችላሉ።
‍

አደጋን እንዴት ማስተዳደርና FOMO ን ማስወገድ ይቻላል? የግብይት ዘይቤዎን ይወስኑ

  • ግልጽ ስትራቴጂ ይኑርዎት። ትኩረት እንዲያደርጉ ያግዝዎታል፤ ከችኮላ ውሳኔም ይጠብቅዎታል።
    ‍
  • አስቀድመው ያቅዱ። ስሜት ጣልቃ ከመግባቱ በፊት ወደ ግብይት መቼ እንደሚገቡና መቼ እንደሚወጡ በትክክል ይወቁ።
    ‍
  • ተለዋዋጭ ይሁኑ። ገበያዎች ሁልጊዜ ይለዋወጣሉ። እቅድን መከተል መልካም ነው፤ አዝማሚያዎችን በጭፍን መከተል ግን አይደለም።
    ‍

የበቀል ግብይትን ይከላከሉ

ስለ በቀል ግብይት (revenge trading) እንነጋገር። ትልቅ ኪሳራ ደርሶብዎት ገንዘብዎን ለመመለስ ተስፋ በማድረግ ወዲያውኑ ወደ ሌላ ግብይት የሚገቡበት ቅጽበት ነው። ሊረዳ የሚችል ነው፣ ግን እምብዛም በጥሩ አይጠናቀቅም።

የበቀል ነጋዴዎች አካሄዳቸውን እንደገና ከመገምገም ይልቅ ተገቢ እቅድ ሳይኖራቸው በቀጥታ ይገባሉ። በስትራቴጂ ሳይሆን በስሜት ስለሚንቀሳቀሱ ብዙውን ጊዜ ከዚያም የባሰ አደገኛ ግብይቶችን ያደርጋሉ። ተጨማሪ አደጋ ተጨማሪ ኪሳራ፣ ተጨማሪ ብስጭት፣ እና እንደገመቱት ተጨማሪ የበቀል ግብይት ያስከትላል። ለመስበር የሚከብድ አስከፊ ዑደት ነው።
‍

የበቀል ግብይትን እንዴት ማስወገድ ይቻላል? የአደጋ አስተዳደር መሳሪያዎችን ይጠቀሙ
‍

Chart illustrating risk management tools with 'Take Profit' and 'Stop Loss' levels, helping traders avoid revenge trading.
  • ስቶፕ ሎስ ያዘጋጁ። ገበያው ከእርስዎ ተቃራኒ ቢንቀሳቀስ ፖዚሽንዎን በራስ-ሰር ይዘጋል፤ ከትልቅ ኪሳራም ይጠብቅዎታል።
    ‍
  • የግብይት ማስታወሻ ደብተር ይያዙ። ስኬቶችዎንና ኪሳራዎችዎን መከታተል ከልምድ እንዲማሩና ስትራቴጂዎን እንዲያሻሽሉ ይረዳዎታል።
    ‍

የግብይት አስተሳሰብዎን ዛሬ ያጠናክሩ

የግብይት ሥነ ልቦናን መቆጣጠር ቻርቶችን እንደመተንተን ወይም የገበያ አዝማሚያዎችን እንደመከተል ያህል አስፈላጊ ነው። ስሜትዎን ማስተዳደር፣ ስትራቴጂዎን መከተልና የአደጋ አስተዳደር መሳሪያዎችን በጥበብ መጠቀም ከቻሉ ለረጅም ጊዜ ስኬት የተሻለ ቦታ ላይ ይሆናሉ።

ታዲያ ለምን ዛሬ አይጀምሩም? በዴሞ ሂሳብ ብልህ ግብይትን ይለማመዱ፣ ወይም ክህሎትዎን ለማሳል በ Deriv Academy ላይ ያሉትን ነፃ ኮርሶቻችንን ይመልከቱ።

ለመጀመር አሁን ባለዎት Deriv ሂሳብ ኢሜይልና የይለፍ ቃል ወደ Deriv Academy ይግቡ።

Quiz

የበቀል ግብይትን (revenge trading) ለማስወገድ ምርጡ መንገድ ምንድን ነው?

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

Analyse markets with AI-powered insights

Explore TradersView
WhatsApp