
በፎሬክስ ግብይት እየጀመሩ ከሆነ፣ ምን እንደሚገበያዩ ማወቅ ያህል መቼ መገበያየት እንዳለብዎት ማወቅም ወሳኝ ነው። ጥብቅ የጊዜ ሰሌዳ ከሚከተለው የአክሲዮን ገበያ በተለየ፣ ፎሬክስ ከሰኞ እስከ አርብ በቀን 24 ሰዓት ይሠራል። ሆኖም ሁሉም ሰዓታት እኩል አይደሉም። አንዳንድ ሰዓታት ከሌሎች የበለጠ ዕድሎችን ይሰጣሉ።
ገበያውን ከአንድ የፋይናንስ ማዕከል ወደ ቀጣዩ እንደሚተላለፍ ዓለም አቀፍ ቅብብል አድርገው ያስቡት። ምድር ስትሽከረከር የግብይት ዱላው ከአንድ ዋና የፋይናንስ ማዕከል ወደ ሌላው ይሸጋገራል። ከሲድኒ ይጀምራል፣ ወደ ቶኪዮ ይሄዳል፣ ከዚያ ወደ ለንደን ይሸጋገራል፣ በመጨረሻም ኒው ዮርክ ይደርሳል። እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የተለየ የገበያ እንቅስቃሴ ያመጣል።
አራቱ ዋና ዋና የፎሬክስ ግብይት ክፍለ ጊዜዎች፦
የሲድኒ ክፍለ ጊዜ (21:00–06:00 (GMT))
እንቅስቃሴው የሚጀምረው እዚህ ነው! የአውስትራሊያና የኒው ዚላንድ ዶላሮች ትኩረት ያገኛሉ። ብዙውን ጊዜ ከማዕበል በፊት እንዳለ መረጋጋት የተረጋጋ ክፍለ ጊዜ ነው።
የቶኪዮ ክፍለ ጊዜ (00:00–09:00 (GMT))
የእስያ ገበያዎች ይነቃሉ፣ የጃፓን የን ደግሞ ዋና ሚና ይይዛል። ይህ ክፍለ ጊዜ በመካከለኛ ፍጥነት ይሄዳል፤ ይህም ነጋዴዎች ይበልጥ ሞቅ ያሉት የለንደንና የኒው ዮርክ ክፍለ ጊዜዎች ከመጀመራቸው በፊት አዝማሚያዎችን እንዲለዩ ያስችላቸዋል።
የለንደን ክፍለ ጊዜ (07:00–16:00 (GMT))
ለንደን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ታመጣለች፤ ዩሮና የብሪታንያ ፓውንድ ጠንካራ እንቅስቃሴ ያሳያሉ። ይህ ለፎሬክስ ግብይት ምርጥ ጊዜ ነው፦ ከፍተኛ ተለዋዋጭነት፣ ትልልቅ ዕድሎችና ብዙ እንቅስቃሴ።
የኒው ዮርክ ክፍለ ጊዜ (12:00–21:00 (GMT))
የአሜሪካ ዶላር ትኩረት ያገኛል፣ ገበያውም በተለይ ከለንደን ጋር ሲደራረብ ይበልጥ ይግለበለባል። ይህ ክፍለ ጊዜ ከፍተኛ ተለዋዋጭነትና የግብይት መጠን ይሰጣል።
የተደራራቢ ክፍለ ጊዜዎች ምትሃት
ከምርጥ የግብይት ዕድሎች መካከል አንዳንዶቹ የሚፈጠሩት ሁለት ክፍለ ጊዜዎች ሲደራረቡ ነው፤ ይህም የግብይት መጠንና ተለዋዋጭነት እንዲጨምር ያደርጋል። እነዚህ ጊዜያት ብዙ ጊዜ ከፍተኛ ተለዋዋጭነትና ፈሳሽነት ያመነጫሉ።
- የለንደንና የኒው ዮርክ መደራረብ (12:00–16:00 (GMT))፦
ከሁሉም የበለጠ የሚጨናነቅና ብዙ ግብይት የሚካሄድበት ክፍለ ጊዜ ነው፣ በተለይ እንደ GBP/USD ላሉ ጥንዶች። ትልልቅ ተጫዋቾች ንቁ ናቸው፣ የዋጋ እንቅስቃሴዎችም ፈንጂ ሊሆኑ ይችላሉ።
- የቶኪዮና የለንደን መደራረብ (07:00–09:00 (GMT))፦
ከለንደንና ኒው ዮርክ መደራረብ ያነሰ ተለዋዋጭ ቢሆንም አሁንም ጥሩ የግብይት ዕድሎችን ይሰጣል።
ጠቃሚ ምክር፦ እነዚህ ክፍለ ጊዜዎች በGMT የሚሰሉ ናቸው፤ ስለዚህ ከእርስዎ የሰዓት ዞን ጋር ያስተካክሏቸው። ከገበያው ጋር ለመጣጣም የሚረዱ ብዙ የኦንላይን መሣሪያዎች አሉ።
የግብይት ሰዓታት ለምን ልዩነት ያመጣሉ
- ለመገበያየት ምርጥ ጊዜዎችን ያግኙ፦ ተለዋዋጭነት ይፈልጋሉ? በለንደን ወይም በኒው ዮርክ ክፍለ ጊዜዎች ይገበያዩ። ረጋ ያለ ፍጥነት ይመርጣሉ? ሲድኒን ወይም ቶኪዮን ይሞክሩ።
- የገበያ ባህሪን ይረዱ፦ የተለያዩ ክፍለ ጊዜዎች የተለያዩ ባህሪያት አሏቸው። የቶኪዮ ክፍለ ጊዜ ብዙ ጊዜ ለመተንበይ የቀለለ ሲሆን፣ የኒው ዮርክ ክፍለ ጊዜ ግን የበለጠ ተለዋዋጭና ተንቀሳቃሽ ሊሆን ይችላል።
- ስልቶችዎን ያቅዱ፦ ስካልፒንግ በቶኪዮ የተሻለ ሊሠራ ይችላል፣ አዝማሚያን የሚከተሉ ስልቶች ደግሞ በለንደን ክፍለ ጊዜ ሊደምቁ ይችላሉ።
አሁን የፎሬክስ ገበያውን ሪትም ስለሚያውቁ፣ ለተሻሉ ዕድሎች የግብይት ክፍለ ጊዜዎችዎን ማቀድ ይችላሉ። ያስታውሱ፣ ጉዳዩ መቼ እንደሚገበያዩ ብቻ አይደለም።
ስኬት ጊዜን በመምረጥ ብቻ አይመጣም። ዕቅድዎን በዲሲፕሊን መፈጸምም ያስፈልጋል። ከግብይት ስልትዎ ጋር የሚስማሙ ክፍለ ጊዜዎችን ይምረጡ፣ አደጋዎን ይቆጣጠሩ፣ ሁልጊዜም በዕቅድ ይገበያዩ።
ዛሬውኑ ወደ Deriv Academy ይግቡና የግብይት ክህሎትዎን ያሳድጉ!
Quiz
የትኛው የፎሬክስ ክፍለ ጊዜ በጣም ንቁ እና ከፍተኛ ግብይት የሚደረግበት ነው?

