
የDeriv P2P ልውውጦችን መሠረታዊ ነገሮች Deriv P2P መድረክ ላይ ከተካኑ በኋላ፣ አፈጻጸምዎን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ማሳደግ የሚወሰነው በየግብይት ስትራቴጂ፣ በጊዜ አመራረጥ እና በእምነት ላይ ነው። አቻ ለአቻ መድረኮች ተለዋዋጭነትን ብቻ አይሰጡም። አስተማማኝ ስምን እንዲገነቡ፣ ገቢዎን እንዲያሳድጉ እና በግብይት ማኅበረሰቡ ውስጥ ዘላቂ ግንኙነቶችን እንዲመሠርቱ ያስችሉዎታል።
የድርድር ችሎታዎን ማሳል ቢፈልጉም ወይም እያንዳንዱን ግብይት ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ ብቻ ቢፈልጉ፣ እነዚህ ልዩ ምክሮች እና ምርጥ ተሞክሮዎች እውነተኛ የP2P ባለሙያ እንዲሆኑ ይረዱዎታል።
የአቻ ለአቻ ግብይቶችዎን ለውጤታማነት በትክክለኛ ጊዜ ማከናወን
የDeriv P2P መድረክ በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት 7 ቀን የሚሠራ ቢሆንም፣ ሁሉም የግብይት ሰዓቶች እኩል ንቁ አይደሉም። የሚገኙ ማስታወቂያዎች ብዛት እና ግብይቶች የሚጠናቀቁበት ፍጥነት ብዙ ጊዜ በጊዜ አመራረጥ ላይ ይወሰናል። ልውውጦችዎን በአካባቢዎ የሥራ ሰዓት ወይም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ባለባቸው ወቅቶች ለማድረግ ማቀድ ፈጣን ምላሽ እና ለስላሳ ግብይቶችን ያስገኛል።
ቅዳሜና እሁድ እና በሕዝባዊ በዓላት ወቅት ገዢዎችም ሆኑ ሻጮች ምላሽ በመስጠት ሊዘገዩ ስለሚችሉ እንቅስቃሴው ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል። ግብይቶችዎን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ባለባቸው ጊዜያት ዙሪያ ማቀድ ጊዜዎን ከመቆጠብ ባሻገር፣ ብዙ ቅናሾች ስለሚገኙ የተሻሉ ስምምነቶችን ለማግኘት ያስችልዎታል።
እርስዎም እንዲሁ በመድረኩ ላይ የሚገኙበትን የሥራ ሰዓት በማዘጋጀት ለሚሆኑ የግብይት አጋሮች መገኘትዎን ማሳየት እንደሚችሉ ልብ ይበሉ።
እንደ P2P አጋር ስምዎንና እምነትዎን መገንባት
ስኬታማ የP2P ልውውጦች ስለ ዋጋ እንደሆኑ ሁሉ ስለ ግንኙነቶችም ናቸው። ከፍተኛ የማጠናቀቅ ምጣኔ መጠበቅ፣ አዎንታዊ አስተያየቶችን ማግኘት እና በሙያዊ መንገድ መመላለስ ሁሉም ለመገለጫዎ ተዓማኒነት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ለግብይት ጥያቄዎች ፈጥነው ምላሽ ይስጡ፣ ግዴታዎችዎን በታማኝነት ይወጡ፣ እንዲሁም በመድረኩ ደህንነቱ በተጠበቀ ቻት ውስጥ በግልጽ ይነጋገሩ።
በጊዜ ሂደት ቁርጠኛ ነጋዴዎች «ተመራጭ አጋሮች» ይሆናሉ። እነዚህ በአስተማማኝነታቸው እና በግልጽነታቸው ምክንያት ሌሎች ከእነሱ ጋር ለመገበያየት የሚጓጉላቸው ተጠቃሚዎች ናቸው። ወጥነት ያለዎት እና ታማኝ መሆንዎ ተደጋጋሚ ደንበኞችን የመሳብ እና የወደፊት ስምምነቶችን የማፋጠን ዕድልዎን ይጨምራል።
ለአቻ ለአቻ ግብይቶች ድርድር እና ዋጋ ማመቻቸት
በአቻ ለአቻ መድረክ መገበያየት ካሉት ታላላቅ መሳቢያዎች አንዱ የራስዎን ዋጋ የመደራደር ዕድል ነው። ሁሉም ስምምነቶች በDeriv ሥርዓት ውስጥ እስከሆኑ ድረስ፣ ከተጓዳኝዎ ጋር ስለ ዋጋ ለመወያየት በመድረኩ ውስጥ ያለውን ቻት ለመጠቀም አይፍሩ።
ተወዳዳሪ ማስታወቂያዎችን ለማዘጋጀት ወይም በነባር ዝርዝሮች ውስጥ ማራኪ ስምምነቶችን ለመለየት የገበያ አዝማሚያዎችን እና የክልሉን አማካይ ዋጋዎች ይከታተሉ። ከትልልቅ የገበያ ለውጦች በፊት የራስዎን ዋጋ ማስተካከል ተጨማሪ ዋጋ ለማግኘት ሊረዳዎ ይችላል፤ በድርድር ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ እና ተለዋዋጭ መሆን ደግሞ ብዙ ጊዜ ስኬታማ እና ተደጋጋሚ ግብይቶችን ያስገኛል።
በDeriv P2P ላይ ክፍያዎችን እና ደህንነትን ማስተዳደር
የDeriv P2P መድረክን መጠቀም ነጻ ቢሆንም፣ አቀራረብዎን ማመቻቸት ከልውውጡ ጋር የተያያዙ ሌሎች ወጪዎችን የበለጠ ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል። የተጓዳኝዎን የምንዛሪ ዋጋ በጥንቃቄ ይመልከቱ እና ከሌሎች ማስታወቂያዎች ጋር ያወዳድሩ፤ ተጨማሪ ክፍያዎችን የሚቀንሱ የአገር ውስጥ የክፍያ ዘዴዎችን ይምረጡ፤ እንዲሁም ልውውጡን ከማረጋገጥዎ በፊት የክፍያ ዘዴው የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች ጨምሮ ሙሉውን ወጪ ሁልጊዜ ያረጋግጡ።
በደህንነት በኩል፣ ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫን (2FA) ማንቃት፣ የይለፍ ቃሎችዎን በየጊዜው ማዘመን እና የሂሳብዎን እንቅስቃሴ መገምገም ገንዘብዎን ይጠብቃል። የክፍያ መረጃዎ ትክክል መሆኑን በየጊዜው መፈተሽም ጥበብ ነው፤ ግንኙነትዎንም ሁልጊዜ በDeriv P2P መድረክ ውስጥ ያድርጉ። ከተጓዳኝዎ ጋር ሌላ ቦታ በፍጹም አይነጋገሩ፣ ሚስጥራዊ ዝርዝሮችንም አያጋሩ።
በDeriv P2P ላይ የመገበያየትን ጥቃቅን ነገሮች መቆጣጠር ለረጅም ጊዜ ስኬት ቁልፍ ነው። በተመቻቸ ጊዜ በመገበያየት፣ ታማኝ ስም በመገንባት፣ የድርድር ክህሎትዎን በማጥራት እና በእያንዳንዱ ደረጃ ለደህንነት ቅድሚያ በመስጠት በDeriv ላይ የአቻ ለአቻ ልውውጦችን ሙሉ አቅም መክፈት ይችላሉ። ብቃትዎን ከፍ ለማድረግ ዝግጁ ነዎት? መሣሪያዎቹን ያስሱ፣ ስትራቴጂዎን ይወስኑ እና በDeriv P2P ማኅበረሰብ ውስጥ ተመራጭ አጋር ይሁኑ።
Quiz
በDeriv ላይ ታማኝ የP2P ልውውጥ አቅራቢ ለመሆን የሚረዳዎት የትኛው አሠራር ነው?


