Deriv MT5ን ማስተዋወቅ
ስለ Deriv MT5 በሚያቀርበው የመግቢያ ትምህርታችን እንኳን በደህና መጡ! ይህ መድረክ ለየልዩነት ውሎች (CFD) ግብይት ዋና መዳረሻዎ እንዲሆን ተዘጋጅቷል፤ የተለያዩ መሠረታዊ ንብረቶችን የዋጋ እንቅስቃሴ ለመገመት ያስችልዎታል። በዚህ ትምህርት የግብይት ጉዞዎን ለመጀመር እንዲረዱዎት የDeriv MT5ን ዋና ዋና ባህሪያት እና ጥቅሞች እንመለከታለን።
የDeriv MT5 አጠቃላይ እይታ
Deriv MT5 የተገነባው በቀላል የተጠቃሚ በይነገጹ እና በላቀ የግብይት አቅሙ በሚታወቀው MetaTrader 5 መድረክ ላይ ነው። ይህ መድረክ ነጋዴዎችን ኃይለኛ የቻርት መሣሪያዎች እና ብዙ አይነት ቴክኒካል አመልካቾች ያስታጥቃቸዋል፤ በዚህም የገበያ አዝማሚያዎችን ተንትነው ስለ ግብይታቸው በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲወስኑ ያስችላቸዋል።
የDeriv MT5 ዋና ዋና ባህሪያት
- ለተጠቃሚ ምቹ ተሞክሮ፦ Deriv MT5 ቀላል እና ግልጽ እንዲሆን ተዘጋጅቷል። ለመጠቀም ቀላል ሆኖ ያገኙታል፤ ስለዚህ አነጋገድን በፍጥነት ተምረው በገበያዎች ውስጥ መጀመር ይችላሉ።
- ጥልቅ የገበያ ትንተና፦ በDeriv MT5 ላይ የሚገኙት የላቁ ቻርቶች እና ቴክኒካል አመልካቾች ስለ ገበያ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ ግንዛቤ ይሰጣሉ። እነዚህ መሣሪያዎች አዝማሚያዎችን ለመለየት እና ሊኖሩ የሚችሉ የዋጋ ለውጦችን ለመተንበይ ይረዱዎታል፤ ይህም የተሻለ የግብይት ውሳኔ እንዲወስኑ ያስችልዎታል።
- የተለያዩ የግብይት አማራጮች፦ መድረኩ ታዋቂ ገንዘቦችን፣ አክሲዮኖችን፣ ሸቀጦችን እና ዴራይቭድ ኢንዴክሶችን ጨምሮ ሰፊ የግብይት መሣሪያዎችን ያቀርባል። ይህ ሰፊ ምርጫ ከግብይት ስልትዎ ጋር የሚጣጣሙ ዕድሎችን ለማግኘት ያስችልዎታል።
- ለፍላጎትዎ ሊበጅ የሚችል ተሞክሮ፦ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ የግብይት ግቦች እና ዘይቤ አለው። Deriv MT5 ይህንን በመገንዘብ ከእያንዳንዱ ሰው የግብይት ምርጫ እና መስፈርት ጋር የሚስማሙ የተለያዩ የሂሳብ አይነቶችን ያቀርባል።
በDeriv MT5 ላይ የሚገኙ የሂሳብ አይነቶች
በDeriv MT5 ላይ ሲነግዱ፣ እያንዳንዳቸው የተለያዩ የግብይት ፍላጎቶችን ለማሟላት የተበጁ በርካታ የሂሳብ አማራጮች አሉዎት፦
- መደበኛ ሂሳብ፦ ለጀማሪዎችም ሆነ ልምድ ላላቸው ነጋዴዎች የሚስማማ ሁለገብ ሂሳብ ሲሆን ተወዳዳሪ ስፕሬዶችን እና የስዋፕ ክፍያዎችን ያቀርባል። ይህ ሂሳብ ሰፊ የመሣሪያዎች ምርጫን ይደግፋል፤ ስለዚህ ለሁሉም አይነት ግብይት ጥሩ ምርጫ ነው።
- ከስዋፕ ነጻ ሂሳብ፦ ለረጅም ጊዜ የግብይት ስልቶች ተስማሚ የሆነው ይህ ሂሳብ የአዳር ስዋፕ ክፍያዎችን ያስቀራል፤ በዚህም ተጨማሪ ወጪ ሳይኖርዎት ፖዚሽኖችን ለረጅም ጊዜ መያዝ ይችላሉ።
- ዜሮ ስፕሬድ ሂሳብ፦ ይህ ሂሳብ ቋሚ የግብይት ኮሚሽኖችን ያቀርባል፤ ስለ ግብይት ወጪዎችዎም ግልጽነት ይሰጣል። በተለይ ተለዋዋጭ ስፕሬዶች የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ለማስወገድ ለሚፈልጉ ስካልፐሮች እና የቀን ነጋዴዎች ጠቃሚ ነው።
- ፋይናንሺያል ሂሳብ፦ በፋይናንስ ገበያዎች ግብይት ላይ ያተኮረው ይህ ሂሳብ ከሚገኙት ሁሉ የጠበቡ ስፕሬዶችን እንዲያገኙ ያስችልዎታል፤ ስለዚህ ለከፍተኛ ድግግሞሽ ነጋዴዎች ተስማሚ ነው።
- ጎልድ ሂሳብ፦ ይህ ሂሳብ በወርቅ እና በከበሩ ማዕድናት ላይ ለመነገድ ያስችላል፤ በዚህ ገበያ ለሚነግዱ ነጋዴዎች ከፍተኛ ዋጋ ለመስጠት የጠበቡ ስፕሬዶችን ይሰጣል።
- ፋይናንሺያል STP ሂሳብ፦ ያለ ኮሚሽን እና ሰፋ ያሉ ስፕሬዶች ያሉት ይህ ሂሳብ ያለ ተጨማሪ የግብይት ክፍያ ቀጥተኛ የገበያ ተሳትፎ ይሰጣል፤ ስለዚህ ለተለያዩ የግብይት ስልቶች ተስማሚ ነው።
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ፣ Deriv MT5 ገና እየጀመሩም ሆነ የግብይት ስልትዎን ማሻሻል ቢፈልጉ የተለያዩ የግብይት ፍላጎቶችን የሚያሟላ ሁሉን አቀፍ መድረክ ነው። ለተጠቃሚ ምቹ በሆነው በይነገጹ፣ በላቁ መሣሪያዎቹ እና በተለያዩ የሂሳብ አይነቶቹ አማካኝነት የግብይት ተሞክሮዎን ከግላዊ ግቦችዎ ጋር እንዲስማማ ማበጀት ይችላሉ።
Deriv MT5ን ለመጠቀም ሲዘጋጁ፣ የመድረኩን ባህሪያት እና የሂሳብ አማራጮች መረዳት ለግብይት ጥረቶችዎ ጠንካራ መሠረት እንደሚሰጥዎ ያስታውሱ። ከኮምፒውተርዎ፣ ከስልክዎ ወይም ከዌብ ብራውዘርዎ Deriv MT5ን እንዴት እንደሚጠቀሙ በምንመራበት በሚቀጥለው ትምህርታችን ይጠብቁን! መልካም ግብይት!
Quiz
Deriv MT5 በዋነኝነት ለምን ጥቅም ላይ ይውላል?
የትኛው የሂሳብ ዓይነት የሌሊት ስዋፕ ክፍያዎችን ያስቀራል?
የZero Spread Account ምን ጥቅም ይሰጣል?


