DBot የግብይት መድረክ
በዚህ ኮርስ የመጨረሻ ትምህርት Deriv Botን እንቃኛለን። ይህ ኮድ ሳይጽፉ አውቶሜትድ የግብይት ስትራቴጂዎችን በቀላሉ ለመፍጠር እና የግብይት ዕድሎችን 24/7 ለመጠቀም የሚያስችል ኃይለኛ መፍትሔ ነው። ቀላሉን «ብሎኮችን» የመጎተት እና የመጣል ባህሪ በመጠቀም በማንኛውም የልምድ ደረጃ ላይ ያሉ ነጋዴዎች ከግብይት ፍላጎታቸው ጋር የሚስማሙ ብጁ ስትራቴጂዎችን መገንባት ይችላሉ።
የDeriv Bot መግቢያ
Deriv Bot ለአጠቃቀም ቀላል እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ነጋዴዎች የፕሮግራሚንግ ክህሎት ሳያስፈልጋቸው የግብይት ስትራቴጂዎቻቸውን አውቶሜት እንዲያደርጉ ቀላል የሆነ በይነገጽ ያቀርባል።
Deriv Botን መጠቀም
Deriv Botን ለመጀመር፦
- በDeriv Trader's Hub ላይ ወደ ሂሳብዎ ይግቡ።
- ወደ Bot Dashboard ለመግባት ከሚገኙት አማራጮች ውስጥ «Deriv Bot»ን ይምረጡ።
ከገቡ በኋላ የግብይት ጉዞዎን ለመጀመር የሚያስችሉ በርካታ አማራጮችን ያያሉ።
የDeriv Bot Dashboard ባህሪያት
ወደ Deriv Bot Dashboard ሲገቡ አራት ዋና ዋና አማራጮችን ያያሉ፦
- ነባር ስትራቴጂዎችን መጫን፦ ስትራቴጂዎችን ከ«My Computer» ወይም ከ«Google Drive» ያስገቡ።
- Quick Strategy፦ አስቀድመው የተዘጋጁ የስትራቴጂ አብነቶችን በመጠቀም የግብይት ቦት ለማስጀመር ፈጣኑ መንገድ።
- Bot Builder፦ ለላቀ ደረጃ ተጠቃሚዎች ከመሠረቱ ብጁ ስትራቴጂዎችን ለመፍጠር ያስችላል።
Quick Strategy
የQuick Strategy ባህሪ እያንዳንዱን የግብይት ቦት በሁለት ዋና ክፍሎች ይከፍላል፦
- የስትራቴጂ አብነት፦ ይህ ቦትዎ ከእያንዳንዱ ግብይት በኋላ በትርፋማነት ላይ ተመስርቶ የስቴክ መጠኑን እንዴት እንደሚያስተካክል ይወስናል።
- የስትራቴጂ አብነቶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- Martingale፦ ወጪዎችን ለማካካስ ከኪሳራ በኋላ ስቴኩን በእጥፍ ይጨምራል።
- D'Alembert፦ ስቴኩን በተወሰነ ዩኒት መሠረት ያስተካክላል፤ ከኪሳራ በኋላ ይጨምራል፣ ትርፍ ከተገኘ በኋላ ደግሞ ይቀንሳል።
- Oscar's Grind፦ አነስተኛ እና ወጥ ትርፎችን በማግኘት ላይ ያተኩራል።
- Reverse Martingale፦ ተከታታይ ትርፎችን ለማሳደግ ከትርፍ በኋላ ስቴኩን ይጨምራል፣ ከኪሳራ በኋላ ደግሞ ይቀንሳል።
- 1-3-2-6፦ ከተከታታይ ትርፎች በኋላ ቋሚ የስቴክ ቅደም ተከተልን ይከተላል።
- Martingale፦ ወጪዎችን ለማካካስ ከኪሳራ በኋላ ስቴኩን በእጥፍ ይጨምራል።
- የስትራቴጂ አብነቶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- የግብይት መለኪያዎች፦ እነዚህ መለኪያዎች የሚነገደውን ንብረት፣ የግብይት አይነት፣ የግዢ ሁኔታዎች፣ የመጀመሪያ ስቴክ፣ የቆይታ ጊዜ፣ የትርፍ ገደብ እና የኪሳራ ገደብ ይወስናሉ።
ስትራቴጂዎን ማዋቀር
የስትራቴጂ አብነትዎን ከመረጡ እና አስፈላጊዎቹን የግብይት መለኪያዎች ከሞሉ በኋላ ቦትዎን ለማስጀመር በቀላሉ «Run»ን ይጫኑ። አካሄድዎን ለማሻሻል እና በራስ መተማመንን ለመገንባት ማንኛውንም ስትራቴጂ መጀመሪያ በዴሞ ሂሳብ ላይ መለማመድዎን ያስታውሱ።
Bot Builderን መጠቀም
ስትራቴጂዎቻቸውን ይበልጥ ማበጀት ለሚፈልጉ Bot Builder የላቁ ባህሪያትን ያቀርባል፦
- Workspace (Canvas)፦ ለቦትዎ ልዩ ተግባራትን ለመፍጠር ብሎኮችን የሚጎትቱበት እና የሚጥሉበት ቦታ ይህ ነው።
- የብሎኮች ምናሌ፦ በግብይት መለኪያዎች፣ በግዢ ሁኔታዎች፣ በሽያጭ ሁኔታዎች እና በግብይት እንደገና የማስጀመር ሁኔታዎች ተመድቧል። እያንዳንዱ ብሎክ ቦቱ እንዴት እንደሚሠራ የሚመሩ ልዩ መመሪያዎች አሉት።
የብሎክ ተግባራት ምሳሌዎች
- የግብይት መለኪያዎች፦ የሚነገድበትን ገበያ፣ የኮንትራት አይነቶችን እና የስቴክ መጠኖችን ይወስናሉ።
- የግዢ ሁኔታዎች፦ ቦቱ በእርስዎ መስፈርቶች መሠረት ወደ ግብይቶች መቼ መግባት እንዳለበት ይገልጻሉ።
- የሽያጭ ሁኔታዎች፦ ግብይቱ ንቁ ሆኖ ባለበት ጊዜ ቦቱ እንዴት መሥራት እንዳለበት ይመራሉ።
- ግብይትን እንደገና የማስጀመር ሁኔታዎች፦ አንድ ኮንትራት ካበቃ በኋላ አዲስ ከመጀመርዎ በፊት ምን መከሰት እንዳለበት ያዋቅራሉ።
ማጠቃለያ
በDeriv Bot ከግብይት ስልትዎ እና ምርጫዎችዎ ጋር የሚስማሙ አውቶሜትድ የግብይት ስትራቴጂዎችን ለመፍጠር የሚያስችል ኃይለኛ መሣሪያ በእጅዎ ላይ አለዎት። Quick Strategyን እና Bot Builderን በመጠቀም በDeriv መድረክ ላይ ሥርዓታዊ የግብይት አካሄድ መመሥረት ይችላሉ።
ወደ ቀጥታ ግብይት ከመሸጋገርዎ በፊት የመረጧቸውን ስትራቴጂዎች ውስብስብ ጉዳዮች መረዳትዎን ለማረጋገጥ በዴሞ ሂሳብ ላይ በደንብ መለማመድዎን ያስታውሱ። በቀጣዩ ትምህርታችን በDeriv ሲንቴቲክ ምርቶች ላይ ኦፕሽኖችን በመጠቀም የግብይት ስትራቴጂዎችን ማስፈጸም እንቃኛለን። በዚህ ትምህርት ላይ ስለተሳተፉ እናመሰግናለን፤ መልካም ግብይት!
Quiz
Deriv Botን የመጠቀም ዋነኛ ጥቅም ምንድን ነው?
የMartingale ስትራቴጂ ምንን ያካትታል?
በ Deriv Bot ውስጥ የግብይት ስትራቴጂዎችን በላቀ ሁኔታ ለማበጀት የሚያስችለው የትኛው ባህሪ ነው?


